አምልኮ ና ስግደት

📌ሥለ አምልኮ እና ስግደት

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይነግረናል?📖

።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

አንዳድ ሰው ማውራት ይቀለዋል

እኔ ደግሞ ሀሳቤን መፃፍ ቀለል ይለኛል።

እነሆ እስኪ ለዛሬ አምልኮ ና ስግደትን ልጋብዛችሁ።

📌አምልኮ📖

።።።።።።።።።።

👉1ኛ.

(ዘጸአት 20፥3-4)

¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯

³ ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይሁኑልህ።

⁴ በላይ በሰማይ ካለው፥ በታችም በምድር ካለው፥ ከምድርም በታች በውኃ ካለው ነገር የማናቸውንም ምሳሌ፥ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ።

👉2ኛ.

(ማቴ 4፥10)

"ለጌታ ለአምላክህ ስገድ እርሱንም ብቻ አምልኩ።"

👉3ኛ.

(1ኛ ቆሮንቶስ 10፥31)

"እንግዲህ የምትበሉ ወይም የምትጠጡ ብትሆኑ ወይም ማናቸውን ነገር ብታደርጉ ሁሉንም ለእግዚአብሔር ክብር አድርጉት።"

📌ስግደት📖

።።።።።።።።።።

👉1ኛ.

(መዝሙረ ዳዊት 95÷6)

" ኑ እንስገድ በፈጣሪያችን በእግዚአብሔር ፊት እንንበርከክ"

👉2ኛ.

(ማቴዎስ 26፡39)

"ጥቂት እልፍ ብሎም በምድር ላይ ወድቆ ጸለየ..."

👉3ኛ.

(ራዕይ 19÷10)

" ልሰግድለትም በእግሩ ፊት ተደፋሁ። እርሱ ግን፡— ይህን አታድርግ፡ አለኝ፡ ለእግዚአብሔር ስገድ፡ አለ።

✏️የግርጌ ማስታወሻ

።።።።።።።።።።።።

👉በ1ኛ ሳሙኤል 15÷22፡-

"መታዘዝ ከመሥዋዕት ይበልጣል። በሚለው ባምንም

👉በማቴ 15÷8-9፡ "እነዚህ ሰዎች በከንፈራቸው ያከብሩኛል ልባቸው ግን ከእኔ በጣም የራቀ ነው።"

እንዳንባልም፣ እጠነቀቃለሁ ፣ እና በእኔ ሕይወትም ሆነ በትውልዴ ልክ

👉በዮሐ 4፥24 እንደተፃፈው፣

📌"እግዚአብሔር መንፈስ ነው የሚሰግዱለትም በመንፈስና በእውነት ሊሰግዱለት ያስፈልጋቸዋል።"

እንደሚል፣ አምልኮ ና ስግደት ለእርሱ ብቻ እና ብቻ የሚል እምነት አለኝ።

።።።።።።።።።።።።

ከዚህ ውጪ፣ የፀጋ፣ የአክብሮት እያሉ ፣ከአብረሃሙ ስላሴ ውጪ ለሌሎች የሚሸራረፍ ስግደት ና አምልኮ አይኖርም ፣አይገባምም። በነጭ ና ጥቀር የተፃፈውም ቅዱሱ መፀሐፍ አያስተምረንም።

።።።።።።።።።።።።

ባጭሩ፣ ከእኔ በቀር ለሌላው አትስገዱ

ከእኔ ውጪ ሌላውን አታምልኩ። የተባልን የአዲስ ኪዳን ልጆች ነን ለማለት እወዳለሁ።

✏️ዳንኤል ወልደፃዲቅ

።።።።።።።።።።።።።።።

2024/12/19 Edited to

... Read morePrayer and worship are central to Christian faith, serving as profound expressions of devotion and connection to God. In the Bible, various passages emphasize the importance of worshiping God in spirit and truth, as noted in John 4:24. Furthermore, worship expands beyond personal reflection; it includes communal gatherings where believers uplift one another through hymns and shared prayers. Incorporating prayer into daily life can transform one’s spiritual journey. Regular engagement in prayer encourages believers to align their hearts with God’s will, as highlighted in Philippians 4:6-7, which reassures that prayer leads to peace that surpasses all understanding. Worship through songs, like the Psalms, reminds individuals of God’s greatness and love, building a strong foundation of faith. The act of worship doesn’t solely refer to singing; it encompasses submission, reverence, and submission in various forms, from quiet meditation to vibrant church services. It’s also a means of experiencing God's presence, fostering a sense of community and belonging within the church. The overall outcome enhances individual faith, unites believers, and strengthens the church body as they navigate their spiritual lives together.