ከ18 አመታት በፊት ስለ ባህር በር (ወደብ) የታየ እና በመጽሐፍ የተጻፈ ትንቢት፥ ራዕይው የተገለጠላቸው የወንጌል አርባኛው ቄስ በሊና ሳርካ ናቸው።
የከፍታ ዘመን ለኢትዮጵያ የሚል መጽሐፋቸው ለመጀመሪያ ጊዜ የታተመው በህዳር ወር 1998 ዓ.ም ነው።
በዚህ መጽሐፍ ገጽ. 4 "እግዚአብሔር ራዕዩን በ1994 ዓ.ም ወደ ባለራዕይው እንደመጣ ባለራይው ይገልፃሉ።
የከፍታ ዘመን ለኢትዮጵያ
" የባቡር መንገዶች"
እግዚአብሔር በማስከተል እንዲህ አሳየኝ። የኢትዮጵያ የባቡር መንገዶች ከጅቡቲ ጋር ብቻ አይሆንም።
በተጨማሪ አራት በር ከኬንያ፣ ሱማሊያ፣ ኤርትራና ሱዳን ጋር ትገናኛ ለች። በዙሪያዋ ያሉትን የባህር በሮች በነጻነት እንድትጠቀም ይሆናል። ከጎረቤቶቿም ጋር ሰላም ይኖራታል።
ያኔ ኢትዮጵያን የጎረቤቶችዋ የምግብ ማዕድ በዙሪያዋ ላሉ አገሮች የበረከት ምንጭ ትሆናለች።
ጎረቤት አገሮች የባህር በራቸውን ለኢትዮጵያ የመክፈታቸው ዋና ምክንያቱ የሰላም መስፈንና የእህል ምርት መገኘት ነው። ኢትዮጵያ የባህር በር ከማግኘቷ ጋር በተያያዘ የብዙ መርከቦች ባለቤት ትሆናለች። በአሁኑ ጊዜ ምን ያህል መርከቦች እንዳሉን ባላውቅም።
ራዕዩ በሚፈጸምበት ወቅት ብዙ መርከቦች ይኖሩናል። ወደ ሞምባሳ የሚሰራው መንገድ ቶሎ እንደሚከናወን ተመለከትኩ። ወዘተ...
እነዚህ እና ሌሎች በመጽሐፉ ውስጥ የተካተቱ ትንቢቶች ይፈጸማሉ።










































































