🎯#የሕይወት #ህግ

።።።።።።።።።።።።።።

💢 #ሰው #አብዝቶ #የሚያስበውን ና #የሚያወራውን #ያንኑ #ነው።

👉ይህ የነጠረ፣የሕይወት ህግ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ በምሳሌ 23፥7 እንዲህ ይላል፦

📖 “በልቡ እንዳሰበ እንዲሁ ነውና፤ ብላ ጠጣ ይልሃል፥ ልቡ ግን ካንተ ጋር አይደለም።”

👉As he thinks in his heart, so is he._

💥 አእምሮህ የሕይወትህ መሪ ነው። የምታስበው ያንተ ማንነት ይሆናል።

📖 በምሳሌ፦ 18፥21 ደግሞ፣ እንዲህ ይለናል፤

💥 “ሞትና ሕይወት በምላስ እጅ ናቸው፤ የሚወድዱአትም ፍሬዋን ይበላሉ።”

— ምሳሌ 18፥21

👉ምን እያለን ነው፣ የምትሉ፣ እህትና ወንድሞቼ፣ ሆይ፦ #የምትናገረው #ቃል #ፍሬ #ያፈራል። #አፉህ #የወደፊትህን #ይዘራል። እና የምትዘራውን ዘር ምረጥ።

👉ቅዱስ ቃሉ፣ በማቴ 12፥34 ላይ ደግሞ እንዲህ አስረግጦ ይነግረናል።

📖 “እናንተ የእፉኝት ልጆች፥ ክፉዎች ስትሆኑ መልካም ለመናገር እንዴት ትችላላችሁ? በልብ ሞልቶ ከተረፈው አፍ ይናገራልና።”

— ማቴዎስ 12፥34

👉ባጭሩ፦#በአእምሮህ #ሙሉ #የሆነውን #አፍህ #ያፈሳል። #አፍህ፣ቃል #ደግሞ #ሕይወትህን ይቀርፃል።

👉 የእግዚአብሔር፣ ቃል፣ በፊልጵ 4፥8 ላይ ደግሞ፣

📖 ፊልጵስዩስ 4

¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯

⁸ በቀረውስ፥ ወንድሞች ሆይ፥ እውነተኛ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ጭምትነት ያለበትን ነገር ሁሉ፥ ጽድቅ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ንጹሕ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ፍቅር ያለበትን ነገር ሁሉ፥ መልካም ወሬ ያለበትን ነገር ሁሉ፥ በጎነት ቢሆን ምስጋናም ቢሆን፥ እነዚህን አስቡ፤

⁹ ከእኔ የተማራችሁትንና የተቀበላችሁትን የሰማችሁትንም ያያችሁትንም እነዚህን አድርጉ፤ የሰላምም አምላክ ከእናንተ ጋር ይሆናል።

👉በዚህ ክፍል፣ እግዚአብሔር አእምሮህን እንድትጠብቅ ያዛል። ለምን? ብለህ ከጠየከኝ፣ #የምታስበው #ያንኑ #ስለምትሆን / #ስለምንሆን /።

🧠 አዕምሮህን፣ ጠብቅ፣ እንዲሁም አሰልጥን።

👉#አዕምሮ → #ቃል → #ድርጊት → #ልማድ → #ባህርይ → #ዕጣ #ፈንታ።

✅ መፍትሄው

።።።።።።።።።።።

፩ኛ. አእምሮህን ጠብቅ

— ሮሜ 12፥2 “አእምሮአችሁ አድሶ ተለወጡ”

፪ኛ. ቃሉን ተናገር

— ኢያሱ 1፥8 “ይህ የሕግ መጽሐፍ ከአፍህ አይለይ”

፫ኛ. ክፉውን ዝጋ

— 2 ቆሮ 10፥5 “ሐሳብ ሁሉ ለክርስቶስ መታዘዝ እንማርከዋለን”

💥በአንድ ዓረፍተ ነገር፣ በአጭሩ፣ ሀሳባችንን፣ እንቋጭና እንሰናበት።

👉 #አፍህ #የልብህ #ድምፅ ማጉያ #ነው። #ልብህ #ደግሞ #የሕይወትህ #መሪ ። እና ብልህ ሁን፣ ቶሎ ንቃ፣ አትዘግይ፣አትቅርም።

💢[ ስለዚህ #የምታስበውንና #የምታወራውን #ምረጥ — #እሱ #ትሆናለህና። ]

።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

© DANIEL W

።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

4/17 Edited to

... Read moreFrom personal experience, I have found that the way we think and speak truly molds our reality and inner self. The biblical references in Proverbs 23:7 "As he thinks in his heart, so is he" and Matthew 12:34 about the fruitfulness of our words resonate deeply with the transformative power of mindset and speech. When I started consciously choosing positive, truthful thoughts and gentle words, my relationships improved, and my outlook on life brightened significantly. The scripture from Philippians 4:8 encourages us to dwell on things that are true, noble, right, pure, lovely, and admirable. Practicing this daily by filtering my thoughts and words helped me develop healthier habits and a character aligned with peace and goodness. It reinforced the idea that our minds lead to our actions, which become habits that define our personality and destiny. Moreover, the sequence mentioned—mind to word, word to action, action to habit, habit to character, and character to destiny—is practically observable. Whenever negative thinking led to harsh words, it usually resulted in poor behavior and strained relationships. Conversely, nurturing positive thoughts led to uplifting conversations and constructive habits. This self-awareness has been key in both spiritual growth and emotional well-being. In modern life, amidst distractions and stress, guarding our mind as Romans 12:2 advises—to be transformed by the renewing of the mind—becomes essential. Meditation on uplifting scripture and mindful speech have served as practical tools to keep my mind healthy and my life focused on meaningful values. Ultimately, this article’s spiritual guidance aligns well with practical living because it pushes us to be vigilant with our thoughts and speech, which strongly influence our life journey. The choice of what seed we plant in our mind and mouth, as Proverbs 18:21 suggests, directly reflects the fruit we harvest in character and destiny.