9.1 ቢሊዮን ዶላር ገቢ፣ 20.7 ሚሊዮን ተጓዥ 150 መዳረሻ የኢትዮጵያ አየር መንገድ✈️
#ethiopianservice *በዛሬው ዕለት ሐምሌ 22/2018 ዓ/ም የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ2018 በጀት ዓመት 9 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቱን የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው አስታወቁ።
አየር መንገዱ የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርቱን አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ፣ የተቋሙን የዕድገት ምዕራፍ የሚያሳዩ አበረታች መረጃዎችን ይፋ አድርጓል።
ዋና ዋና የሥራ አፈጻጸም ነጥቦች፡
✈️አጠቃላይ ገቢ:- በበጀት ዓመቱ 9 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱ ተገልጿል።
👉ተጓዦች እና ጭነት:- አየር መንገዱ አጠቃላይ 20 ነጥብ 7 ሚሊዮን ደንበኞችን ማጓጓዝ የቻለ ሲሆን፤ በጭነት መጓጓዣ በኩልም 897 ሺህ ቶን ጭነት ማጓጓዝ ችሏል።
የበረራ መዳረሻዎች✈️🌟
✈️4 አዳዲስ ዓለም አቀፍ መዳረሻዎችን በመጨመር አጠቃላይ ዓለም አቀፍ መዳረሻዎችን ወደ 150 አድርሷል።
✈️3 የሀገር ውስጥ መዳረሻዎችን በመጨመር የሀገር ውስጥ መዳረሻዎችን ቁጥር ወደ 25 አሳድጓል።
👉የፍሊት እና ቴክኖሎጂ ዝማኔ:- በዓመቱ 9 አዳዲስ አውሮፕላኖች በግዥና በኪራይ የገቡ ሲሆን፤ በተጨማሪም 8 የፓይለት ማሰልጠኛ አውሮፕላኖች ተገዝተዋል።
👉የመሠረተ ልማት ግንባታዎች:- የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ተርሚናልን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች ሰፊ የመሠረተ ልማት ማስፋፊያ ሥራዎች በመከናወን ላይ ይገኛሉ።
Ethiopian Airlines
#EthiopianAirlines #Aviation #BusinessGrowth #Ethiopia #AfricaAviation #Travel #News #AfricanAirlines



























































































