በደም የታተመ (PRINTED IN BLOOD)
በደም የታተመ ( Printed in blood )
።።።።።።።።።።።
ዳግም ላልመለስ፣
ወደ ትላንትና
አጥብቄ እይዛለሁ፣
መዳኔን በፀና
ዳገቱን ያለፍኩት
በጌታ ፀጋ ነው
ሌሊቶቼ የነጉት
አምላክ እረድቶኝ ነው ።
አሁን፣እምነት አለኝ
ዳገትን አልፈራም፣
ደግሞም ፡ አይገጥመኝም
ድቅድቁ ጭለማም ከቶ
አይጠብቀኝም።
የደከመ አጥንቴ፣
በርትቶልኝ፣ አየሁ
የልቤ ብረሃን
ላይጠፋ በርቶልኝ ።
ይሔን እንቁ እውነት
አልጥለውም ላፍታ
ከቶ አልዘነጋውም።
በማዕበሉ ዳግም
አልሰጥምም ፣ አ ምናለሁ።
የእምነት አዋጅ አለኝ
ትውልዱ፣ ይስማልኝ፤
ዘላቂ ነው ደስታዬ፣
ዘላለም ነው ሕብረቴ
በደም ስለዋጀኝ፣
መልካሙ አባቴ።
ክሴ ተሰርዟል፣
ኩነኔ የለብኝም
የዳንኩት፣ በእምነት ነው
ከእኔ አንዳች የለም።
እንዳይካኝ ከቶ
እንዳይበላኝ፣ ጠላቴ
በደም የታተመ የደም ዋጋ አለብኝ
ይታያል ከፊቴ።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።
©Daniel W.
Dec 08/2024
።።።።።።።።።።።።።።።።።።
“ደግሞም ያተመን የመንፈሱንም መያዣ በልባችን የሰጠን እርሱ ነው።”
— 2ኛ ቆሮ 1፥22
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።



























