📌እንኳን፣ ለጌታች እና ለድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በአል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን።
ፍሲካ እና ትንሳኤ
።።።።።።።።።።።
🎯ሁለቱም ያንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ናቸው።
👉ፋሲካ፣ ክብረ በአሉ ሲሆን
👉ትንሳኤው ደግሞ ጌታችን ሞቶ በሦስተኛው ቀን ሞትን አሸንፎ የተነሳበት፣ እርሱ ሂደት ነው ትንሳኤው የምንለው።
🎯በማቲዎስ ወንጌል 26÷57-68
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።። እንደምንመለከተው፦ ሙሉ ክፍሉን እናንተ እንድታነቡት፣ እየጋበዝኩ፣ እኔ ወደ ምፈልገው ሀሳብ ልውሰዳችሁ።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ጻፎች እና ሽማግሌዎች ኢየሱስን፣ ይዘው፣ ወደ ሊቀ ካህናቱ ግቢ፣ እንዲገደል በመፈለግ ሲያቀርቡት እንመለከታለን።
ይሔ ሁሉ ክስ እና ክህደት ተፈፅሞበት ነገሩ አልተቋጨም፣
👉ቀያፋ እና ስሞኦን
👉 ዳኛው ጲላጦ ፊት፣
ፍርድን እንዲሰጥ አቀረቡት፤
👉ጲላጦስ ንፅህናውን እያወቀ ሥርአቱ በልጦበት፣ ይገደል ዘንድ፣#ፈርዷል።
ነገር ግን፣
🎯በመስቀሉ አናት ላይ፣
#እየገደሉት #ያሉት #ማን #እንደሆነ #መስክሮለታል።
እሱም...
(👉የአይሁድ ንጉስ የናዝሬቱ ኢየሱስ፣ የሚል ነበረ።)
ይሔኔ፣ እኔ ደግሞ፣ የቀያፋ እና ሶሞን ዱለታን፣ እንዲህ አልኩት፦
🎯ለፍርድ፣እያቆሙ
።።።።።።።።።።።።።።
ቀያፋ እና ሰሞኦን፣
ግብራቸው ሰመረ
በአብሮነት፣ ታደሙ፣
ለእርድ ያዘጋጁት፣
በጲላጦስ ችሎት
ለክስ፣ እያቆሙ፣
ለፍርድ እያቆሙ።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
👉እንኳን፣ ለጌታችን እና ለድሃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ መታሰቢያ በዓለ በሰላም አደረሳችሁ።
።።።።።።።።።።።።።።።።
📌ሰማይን የፈጠረ፣ ምድርን የዘረጋ
ከስላሴ፣ አካል፣ አንዱ የሆነው ኢየሱስ ተጠማሁ፣ ሲል ተደመጠ።
****
👉ለዚህ፣ጌታ፣ ሁሉ በሁሉ ለሆነ ንጉስ፣#ጥሙን #ይቆርጥበት፣ ዘንድ ውሃ አልሰጡትም፣
በምትኩ የተሰጠውን ከቅዱስ ቃሉ ላንብብላችሁ።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
📖ዮሐንስ 19÷28-30
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁸ ከዚህ በኋላ ኢየሱስ አሁን ሁሉ እንደተፈጸመ አውቆ የመጽሐፉ ቃል ይፈጸም ዘንድ፦ #ተጠማሁ #አለ።
²⁹ በዚያም ሆምጣጤ የሞላበት ዕቃ ተቀምጦ ነበር፤ እነርሱም ሆምጣጤውን በሰፍነግ ሞልተው በሁሶፕም አድርገው ወደ አፉ አቀረቡለት።
³⁰ ኢየሱስም ሆምጣጤውን ከተቀበለ በኋላ፦ #ተፈጸመ አለ፥ ራሱንም አዘንብሎ ነፍሱን አሳልፎ ሰጠ።
።።።።።።።።።።።።።።።።።
👉 ይሔንን፣ ክፍል ሳነብ በጣም ተደመምኩ፣ እንዴት ውሃን ለፈጠረ፣ ቆምጣጤ ይሰጡታል ብዬ?
📌እኔ ደግሞ፣ ከዚህ ቀደም እንደነገርኳችሁ፦ ስሜቴን በብዕሬ ለመግለፅ ምክኒያት እፈልጋለሁ እና የኢየሱስ፣ መጠማት ውስጤ ሲመላለስ
እንዲህ አልኩ፦
#2 ኛ
🎯ውሃ ጠማኝ
።።።።።።።።።።።
በባረካት፣ ምድር
ፀጋ ባልነጠፈ
የወይን ምንጭ፣ አገር
በተትረፈረፈ
በፀሐፍት፣ ጎጆ
ጠጅ እየጎረፈ
ውሃ ጠማኝ ባለ፣ ኮምጣጤ አተረፈ።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ይሔ ሁሉ የሆነው፣ ትንቢቾች ይፈፀሙ ዘንድ እና የሰው ልጅ ከአባቱ ጋይ ይታረቅ ዘንድ ነው።
👉 ይሔን ሳስብ ደግሞ፣ እንዲህ አልኩ
#3 ኛ
🎯ፍፃሜ
።።።።።።።።።።።።
የብሉይ፣ፍፃሜ
የአዲስ፣ ሕይወት
ኢየሱስ፣ክርስቶስ ፣
የዓለም መድሐኒት።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
🎯 #4 ኛ
የፍቅር ገድል
።።።።።።።።።።።።
የፍቅር፣ቱባው
ሲተረተር
ገድለ ምንዥላቱ፣
ሲደረደር
አንድያ ልጁን፣
ማሳለፍ
እንዲገደል፣
እንዲሰየፍ።
።።።።።።።።።።።።።።።
“በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።”
— ዮሐንስ 3፥16
።።።።።።።።።።።።።።።።።።
#5 ኛ
🎯ሕይወት
።።።።።።።።።
በትንሳኤው፣ ጉልበት፣
ያልሆነ ምን አለ፣
ሙት ማንነታችን፣
ሕይወት ተቀበለ
እዳ፣ ተከፈለ።
ባርነት፣ አበቃ
ሞታችን፣ተሻረ
ሙት፣ ማንነታችን
ሕይወት፣ ተካፈለ።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
#6 ኛ፦
🎯የሚራራ፣
።።።።።።።።።።
ያለ እጅ መንሻ፣
ምህረት፣ የሰጠ
የሚራራ፣አምላክ
ከሁሉ የበለጠ።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
“ፍቅርም እንደዚህ ነው፤ እግዚአብሔር እርሱ ራሱ እንደ ወደደን ስለ ኃጢአታችንም ማስተስሪያ ይሆን ዘንድ ልጁን እንደ ላከ እንጂ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው አይደለም።”
— 1ኛ ዮሐንስ 4፥10
።።።።።።።።።።።።።።።
በድጋሜ እንኳን ለትንሳኤው መታሰቢያ አደረሳችሁ እያልኩ፣
🎯 #አምላክችን፣#ሕያው #ነው #እንደ #ሞተ #አልቀረም። #ተነስቷል፣ #ደግሞ #ዳግመኛ #ተመልሶ #ይመጣል።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
©ዳንኤል ወልደፃዲቅ
2025
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
































































































