✍በአንድ አገር የሚኖሩ በጣም የሚዋደዱ ና የሚከባበሩ ሁለት ጓደኛሞች ነበሩ። ሁለቱም የየራሳቸው እምነት እና ሙያ ነበራቸው።
በሙያቸው አንዱ ያንዱን ከማድነቅ ና እውቅና ከመስጠት ቦዝነው አያውቁም።
✍በእምነታቸው ላይ ግን የጫማና ኮፍያ ያህል እርቀት እና ልዩነት ይታይባቸዋል፤ በወዳጅነታቸው መካከል ግን ንፋስ አይገባም ከሚባሉት ተምሳሌቶች ምዕራፍ ይመደባሉ።
✍ አንደኛው በሙያው ሰዓሊ ና ገጣሚ ሲሆን በስሎቹ ና በሚፅፋቸው ግጥሞቹ አንቱታን የተቸረ ሰው ነው። ሁለተኛው ግለሰብ አንቱ የተባለ (የኬሚስት) ባለሙያ ነው።
በሁለቱ መካከል ፦ሰዓሊው ና ገጣሚው እግዚያብሔር አለ የሚል እምነት አራማጅ እና አማኝ ነው። (የኬሚስት)ባለሙያው ግን እግዚያብሔር ብሎ ነገር የለም፤ ብሎ የሚያምን (ኤቲስት)። *
✍እዚህ ላይ እግዚያብሔር አለ ወይ የለም ብሎ ማመን ሁለቱም እምነት ነው። አንዱ የለም ሌላኛው አለ በማለት ሁለቱም ያምናሉና።
✍ወደተነሳሁበት ተመልሻለው፤ የኬሚስትሪ ባለሙያው ሰዓሊ ና ገጣሚ ወዳጁን ባልተለመደ ሁኔታ " ሁሌ የሚገርመኝ ያንተ የወዳጄ ሞኝነት ነው፤
You are So Foolish እንዴት እግዚያብሔር አለ ብለህ ታምናለህ በጣም ቅዠት እኮ ነው።
እስኪ አስበው የት አለ?
አይጨበጥ፣አትዳስሰው፤
ወይ አታየው
ኧረ ቆም ብለህ አስብ እንደተማረ ፊደል እንደቆጠረ ሰው"
*ሰዓሊውና ገጣሚው ለተወሰነ ጊዜ አሰበና ምንም ክፉ ሳይወጣው ፡"ለዛሬ ይብቃን ይሔን ጉዳይ ግን አልቋጨነውም እና ነገ ምሳ ሰዓት ላይ እኔ ቤት ምሳ እየበላን እናወጋለን መልካም ጊዜ ይሁንልህ" ብሎ ተሰናበተው።
✍ሰዓሊና ገጣሚው ለሊቱን ሙሉ መተኛት አልቻለም ሥለ ህልውናው፣ ማንነቱ በተዋቡ ቃላት ብዕሩን ከወረቀት ያዋህድ ና ይቀኝ ጀመር ።
ወዲህ ደግሞ የስል ሸራውን ወጥሮ ቀለሙን በጥብጦ ተፈጥሮን እና ሞላዋን በተረዳው እና ባስተዋለው ልክ ስሜቱ የመራውን ያህል የተለያዩ ስዕሎችን እየሳለ ስሎቹን በሥነ -ግጥም እያስደገፈ የስዕል ሸራውን( ካንቫስ )
በተዋቡ ና አግራሞትን በሚጭሩ ስዕሎች ሞላቸው።
* ✍መድረስ አይቀር ና የምሳ ሰዓቱ ደረሰና እግዚያብሔር የለም ባዩ በቀጠሮው ቦታ ተገኘ።
የወዳጁ ቤት ፍፁም ተለውጧል፤ ማመን ከበደው ሰላምታም አልሰጠው በፀጥታ ተውጦ እና በአግራሞት ተሞልቶ ካንደበቱ ቃላት እያጠረው እያገላበጠ ሲለው ወደ አፍንጫው እያስጠጋ እያሸተተው፣ ከብዙ ዝምታ በሓላ
*✍ እኔ ምለው! ማነው እነዚህን የመሳሰሉ ግሩም እና ድንቅ ስዕሎች የሳላቸው ማነው?
ሲል ይጠይቃል።
ሰዓሊና ገጣሚው " አይ ማንም የሳላቸው ሰው የለም እንዲሁ አለ አይደል በዝግመተ ለውጥ ቀዮ ከቢጫው ቢጫው ከሀምራዊው አየተባለቀ አንዱ አንዱ ላይ እየተደረብ ይሔንን መሳይ ስዕል ተፈጠረ ብሎ መለሰለት።"
✍ይሔኔ እግዚያብሔር የለም ባዮ ተናደደ ወንበር ይደበድብ ና እቃን ከእቃ ጋር ማጋጨቱን ተያያዘው፤
(You are despiteing me!) እየሰደብከኝ ነው፤
እያለ ለያዥ ለገራዥ አሸገረ።
✍ይሔኔ እግዚያብሔር አለ ብሎ የሚያምነው በተረጋጋ ማንነት "ወንድሜ ተረጋጋ እኔ ከልቤ እወድሃለው: ብሎም አከብርሃለው።
✍ነገር ግን ይሔን ያልከኝ አንተ ነህ ' ነገሮች በዝግመተ ለውጥ መጡ፣ተገኙ እንጂ ፈጣሪም ተፈጣሪም ብሎ ነገር የለም' ብለህ።
✍ዛሬ ከሁኔታህ የምረዳው ከእነዚህ ውብ ስዕሎች ጀርባ ማን እዳበጃቸው ማን እንደሳላቸው ባለቤታቸውን ስትፈልግ ነው።
✍ ልብ በል ይሔን በሰው እጅ የተሳለ ስዕል አይተህ በአግራሞት ተሞልተህ ማን እንደሰራቸው ለማወቅ እንደተነሳህ ሁሉ ይሔን ውስብስብ አለም በሰማይ እና የብስ እንዲሁም በባህር (Colour Full) የሆኑ ታይተው የማይጠገቡ ፍጥረቶችን ስትመለከት እንዴት ባለቤት አልባ ፡ወፍ ዘራሽ ሆነው ታዩህ?
***
🙏 እስኪ አንዴ አስተውል
በዱር በገደሉ ያሉትን አዕዋፍ ፤
ወቅያኖሱን እየው ፡በተሰባጠረ
ባማረ መልካቸው
ማነው ያሳመራ
ማንስ ፈጠራቸው?።
***
ሥለዚህ ወንድሜ፦
እግዚያብሔር አለ፤🙏
🙏 ለፍጥረት ውበትን እያጎናፀፍ።🙏
🙏እርሱ ሰማያትን በቃሉ ያፀና
በመንፈሱ ውበት አልፋ ነው ገናና።🙏
✍በዚህ አጋጣሚ እውቀት ከሚመስል
ከከሃዲ መንፈስ
ጠብቅ እራስህን ቆም ብለህ መልስ።
🙏እርሱ፦ዛሬ
"አንተ" ተብሎ
ነገ
"አንቱ "የማይባል🙏
አልፋ ነው ኦሜጋ ዘላለም ዘ ... ላ'... ለ'...ም
ሰው ይለወጥ እንጂ እርሱ አይለወጥም።
መጀመሪያ ና መጨረሻ የሌለው
አብረሃም ሳይወለድ እኔ አለሁ እያለ
ብቻውን ያለ ና የሚኖር (ያህዌ) ያው ነው።
ዘላለም ኗሪ ነው።
🙏ለዛሬ በዚሁ ይብቃኝ
ልሰናበት
እውቀት ከሚመስል ከካህዲ መንፈስ
ጠብቅ እራስህን ቆም ብለህ መልስ ።🙏
።።።።።።።።።።።። ከሁለቱ ጓደኛሞች የቀረላችሁ ነገር ካለ እሰየው፣ ያለበለዚያ ግን ስላደከምኳችሁ ይቅርታ።።።።
########//////######
ዳንኤል ወልደፃዲቅ( ወርቅነሽ ) ነኝ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።















































































