በአንድ ንጉሥ ተጀምሮ፣ በዘጠኝ ሥርዎ መንግሥታት ተከናውኖ በ2 ሺህ 3 መቶ ዘመናት የተጠናቀቀው የትውልድ ቅብብሎሽ ፅናት ማሳያው ታላቁ ግንብ ሰው አልሠራውም እስኪባል ድረስ የምህንድስና ጥበቡ እና ዓላማው ዛሬም ዓለምን ያስደንቃል።
በእርግጥ ዛሬ ላይ ቻይና ከዓለም ሁለተኛውን ግዙፍ ኢኮኖሚ ገንብታ በዓለም የልዕለ ኃያልነት መንበር ላይ መቀመጧን ለተመለከተ ስለዕድገቷ ምስጢር ብዙ ርቀት ሳይጓዝ የሚያያቸው ምክንያቶች እልፍ ናቸው።
ከብዙዎቹ ምክንያቶቹ አንዱ እና ዋናው የረጅም ጊዜ በትውልድ ቅብብሎሽ ውስጥ ያለፈ የስልጣኔ እርሾ ያላት መሆኗ “እየደመሰሱ መቅዳት” የሚለውን መርህ በጥበብ ማለፏ ለዛሬ እድገቷ ምስጢር ዋናው መሆኑን መገመት የሚከብድ አይደለም።
ይህን ምስጢር ለማረጋገጥ ደግሞ በ2 ሺህ 300 ዓመታት በዘጠኝ ሥርዎ መንግሥታት የመጣው መሪ ሁሉ አሻራውን አሳርፎበት የትውልድ ፕሮጀክት የሆነው ታላቁ የቻይና ግንብ ዛሬም ሕያው ምስክር።
ታላቁ የቻይና ግንብ በወቅቱ ቻይናውያን ራሳቸውን ለመከላከል ያስፈልጋል ብለው ብዙ መክረውበት የጀመሩት በመሆኑ ነገሥታቱ ሁሉ ሲቀየሩ በአስፈላጊነቱ ላይ ጥያቄ ስላልነበራቸው የሁሉም ዓላማ ግንቡን ማጠናቀቅ ላይ ሆኗል።
ግንባታው ሁለት ሺህ ዓመታትን የፈጀው እና በትውልዶች ፅናት ለውጤት የበቃው ታላቁ የቻይና ግንብ ከግንባታው ግዝፈት የተነሳ “ድራጎን” አግዟቸው ካልሆነ በቀር በሰው ልጅ አቅም ይህን መስራት አይቻልም እስኪባል ድረስ አስደናቂ ሆኗል።
የቻይና ግንብ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ በነበረው ጊዜ ዓለም ሲሚንቶን አልፈጠረችም ቻይናም ይህን አታውቅም፤ እናም ቻይናውያን ይህንን ግንብ የገነቡት ከሩዝ ዱቄት እና ከኖራ ጋር ቀላቅለው በፈጠሩት እንደ ሲሚንቶ ያለ ውኃ የማያስገባ ማጣበቂያ በመጠቀም ነበር።
ለመሆኑ በዘመናት ውስጥ መሪዎች ሲቀያየሩ ጭምር የሀገር ምልክት የሆነውን ታላቁን የቻይና ግንብ ከመገንባት አልቀረም። የሀገር ርዕይ በትውልድ ቅብብሎሽ ሲፈጸም እንዲህ ነው የሚያስብል ሆኗል ዛሬ። ሙሉውን በኮሜንት ሲክሽን ውስጥ ባለው ሊን ክ ያንብቡ፦




























































