👉ብዙ ጊዜ በምሳሌ ማስተማር እና ማስረዳት የሚወደው የአለማችን የማይደገመው መምህር፣ ኢየሱስ ክስቶስ በማቴዎስ 7፡13÷14
እንዲህ አስተማረ፣ ወደ ጥፋት ከሚወስደው “ሰፊ ደጅ” በተቃራኒ “ጠባብ በር” አስቸጋሪ የሆነውን የሕይወት ጎዳና ፍንትው አድርጎ አሳያቸው።
📌 ጠባቡ በር የእውነተኛ ቅድስና ሕይወትን፣ ለመታዘዝ መጣርን፣ እና በክርስቶስ ላይ ማመንን ሲያመልክት፣ ይህም ሆን ተብሎ እና ፈታኝ የሆነ፣ ውጤቱም የወሰኑ ፣የቆረጡ ና ምርጫቸውን ከምርጫው ጋር ያደረጉ “ጥቂቶች ብቻ የሚያገኙት” እንደሆነ ማሳያ ነው።
📖ማቴዎስ 7
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹³ በጠበበው ደጅ ግቡ፤ ወደ ጥፋት የሚወስደው ደጅ ሰፊ፥ መንገዱም ትልቅ ነውና፥ ወደ እርሱም የሚገቡ ብዙዎች ናቸው፤
¹⁴ ወደ ሕይወት የሚወስደው ደጅ የጠበበ፥ መንገዱም የቀጠነ ነውና፥ የሚያገኙትም ጥቂቶች ናቸው።
።።።።።።።።።።።።
📌የግርጌ ማስታወሻ፣
።።።።።።።።።።።።።
በህይወት ውስጥ ጥንቃቄ የተሞላበት ምርጫ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን አስተማረ።
📌"ጠባቡ በር" ጥረትን፣ ራስን መግዛትን እና ለመንፈሳዊ እሴቶች ቁርጠኝነትን የሚጠይቅ፣ ወደ ዘላለማዊ ህይወት የሚመራውን መንገድ ያመለክታል።
📌በአንጻሩ ደግሞ "ሰፊው በር" የቀላል እና የዓለማዊ ምኞቶችን መንገድ ያመለክታል፣ ነገር ግን በመጨረሻ ወደ ጥፋት እንደሚያመራ አልሸሸገንም።
📌ይህ ትምህርት ቅድሚያ በምንሰጣቸው ነገሮች እና በየቀኑ በምናደርጋቸው ምርጫዎች ላይ ማሰላሰልን አስተዋይነትን ያበረታታል።
📌ሆን ብለን ለመኖር እና ከእምነታችን ወይም መልካም እሴቶቻችን ጋር ጥልቅ መረዳት እንዲኖረን እድል ይሰጣል።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
👉እነሆ እኔ ደግሞ፣ እንዲህ ልበል
🎯 ጠባቡ፣በር
።።።።።።።።።።።።።።።
አይንህን፣ ጨፍነህ
ወደ ውስጥ ስታስብ፣
ሰፊ መንገድ መሃል፣
ጠባቧን ካስተዋልክ
አንተ፣ አትራፊ ነህ፣
በሕይወት ተርፈሃል
በመርከቡ፣እንዳለህ ፣
መልህቅ ይዞሃል።
ይሔ ካልተሰማህ፣
ጎዳናው ከሰፋህ
ተመለስ በጊዜ፣
ጀንበር ሳይጠልቅብህ
ጠባቧን ምረጣት፣
ሰፋፊው ግን ይቅርብህ።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
© ዳንኤል ወልደፃዲቅ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።







































































































